በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ቤተክርስቲያን በናያጋራ አካባቢ፡ ካናዳ/ Kidus Yohannes Weldenegodguad Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Niagara Region, Canada
Programs & Events
ኑ የእግዚያብሔርን በረከት አብረን እንካፈል! Come, let us share in the blessings of God!
የሚቀጥለው ጉባኤያችን ቅዳሜ, መስከረም 24,2018 ዓ. ም. (October 04,2025) ከጠዋቱ 11 ሰዓት (5 AM) ጀምሮ ነው። በእለቱ ብፁዕ አባታችን አቡነ ዲሜጥሮስ፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምስራቅ ካናዳ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ሰባኪያነ ወንጌል እና የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማሪያን በሚታደሙበት ጉባኤ ለአካባቢያችን የመጀመሪያ የሆነውን የቅዳሴ አገልግሎት ይጀመራል። ወዳጅ ዘመዶችዎን በመጋበዝ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል። ታሪካዊ የሆነ ጉባኤ በመሆኑ የታሪክ ተካፋይ እና መስካሪ ይሁኑ።
Our upcoming liturgy will take place on Saturday, October 4, 2025, at 5:00 AM. On that day, His Holiness Abune Demetrios, the Archbishop of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church of Eastern Canada and Surrounding Areas, will lead the first-ever Mass service (Kidase) for our community, with priests, deacons, evangelists, and Sunday school choirs participating. We invite your friends and family to join us and share in this blessing. As this is a historic moment, be part of history and witness this special event.

ቦታ/Venue፡ St. Gregory The Illuminator Armenian Apostolic Orthodox Church, 49 Carlton St, St. Catharines, ON L2R 1P7
የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኝ ከሆኑ እና በናያጋራ አካባቢ የሚኖሩ ከሆነ የቤተክርስቲያናችን አባል ለመሆን የሚከተልውን ፎርም ይሙሉ።
If you believe in and follow the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church and live in the Niagara Region, please complete the following form to join our church.
News and Views
ሆሣዕና/ Palm Sunday
ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፥ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፥ ተቀመጠበትም።
ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር።
የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤
በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።
የማ. ወ. ፲፩: ፯-፲
የሚያዝያ አራቱ ጉባዔያችን በብዙ መልኩ ለየት ያለ ነበር። የወሩ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ከመሆኑም ባሻገር፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ልጆች እና አዋቂዎች መዝሙር አጥንተው በታዳሚ ፊት እግዚያብሔርን ያመሰገኑበት፣ ሆሳእና በአርያም እያሉ የዘምሩበት፣ ሆሳእናን ያከበርንበት ልዩ ቀን ነበር። ለአባቶች ክብር እና ምስጋና ይድረሳቸውና የሚከተሉት ፎቶች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚመሰክሩት፡ ሆሳእናን ደመቅ ባለ መልኩ አክብረናል።
Our assembly on April 12, 2025, showcased numerous firsts. Both children and adults studied hymns for the first time and praised God before the congregation. As shown in the following photos and videos, with the help of our esteemed fathers, we celebrated Hosanna (palm Sunday) to its fullest extent.










ቤተክርስቲያናችን ነዋየ ቅዱሳት ተበረከቱለት/ Our Church Received Donations
ቤተክርስቲያናችን ኢትዮጵያም፣ ካናዳም በሚገኙ ምእመናን እና ወዳጆች አማካኝነት በርከት ያሉ እና የተለያዩ ንዋየ ቅዱሳትን በስጦታ ተበርክቶለታል። ንዋየ ቅዱሳቱን በመግዛት፣ በማጓጓዝ እንዲሁም ገንዘባቸውን አውጥተው ግዚያቸውን ሰውተው ንዋየ ቅዱሳቱ በእጃችን እንዲገባ ለተባበራችሁ፣ በጸሎታችሁ ላሰባችሁ፣ በሃሳብ ለረዳችሁ፡ በታላቁ እግዚያብሔር ስም እናመሰግናችኋለን። እግዚያብሔር በረከቱን በቤታችሁ ያግባላችሁ። የሚከተለው ተንቀሳቃሽ ምስል መጋቢት 6, 2017 (March 15, 2025) ባደረኘው ጉባኤ ንዋየ ቅዱሳቱ ሲባረኩ፣ ለጋሾች ሲባረኩ ያሳያል።
Our Church has received a variety of sacred relics from believers and friends in Ethiopia and Canada. We express our gratitude in the name of Almighty God to those who generously donated their money and resources to purchase and transport the sacred relics. We also thank those who support our church through their prayers and thoughts. May God bring His blessings into your home. The following video shows the moment when Fathers bless the sacred relics and donors during our March 15, 2025, assembly.